Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የመሰረዝ ዕቅድ ለራሷ ኩባንያዎችም አስደንጋጭ ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የመሰረዝ ዕቅድ ለራሷ ኩባንያዎችም ያልተጠበቀና አስደንጋጭ ሆኗል።

አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ በጥር ወር መጀመሪያ ለማስውጣት ዕቅድ እንዳላት ማስታወቋን ተከትሎ በአሜሪካ የአልባሳት እና ጫማ ኢንዱስትሪዎች ዘንድ መደናገጥን ፈጥሯል ተብሏል።

የአሜሪካ አልባሳት እና ጫማ ማህበር የቦርድ ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሪክ ሄልፌንቤይን በፎርብስ መጽሄት ሃሳባቸውን አስፍረዋል፡፡

ሪክ ሄልፌንቤይን በመጽሄቱ ባሰፈሩት ሃሳብ፥ ኢትዮጵያን ከአጎዋ ማስወጣት የሚለው ሃሳብ በራሱ ትልቅ ስህተት ነውም ይላሉ።

አሜሪካ የአልባሳት እና የጫማ ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋይ እንዲያፈሱ ማበረታታቷን አስታውሰው የአሁኑ ውሳኔዋን ያልተጠበቀ እና ተገቢ ያልሆነ ብለው፥ እንዲሁም ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ባለችበት ወቅት መሆኑን አጥብቀው ኮንነዋል፡፡

በተጨማሪም ይህ ያልተጠበቀ ፣ ነገሮችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ ከሰሃራ በታች የአፍሪካ አገራት በሚገኙ ሌሎች ባለሃብቶች ላይም ፍርሃት ፈጥሯልም ነው ያሉት ሪክ ሄልፌንቤይን ።

አያይዘውም፥ እውነቱን ለመናገር፣ አጎዋ ዩናይትድ ስቴትስ ከፈጠራቸው የንግድ መርሃ ግብሮች ሁሉ የተሻለ አይደለም፣ ሆኖም ግን ብዙ ታዳጊ አገሮች ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል።

ሆኖም ለ21 ዓመታት የአጎዋ አፈጻጸም በተወሰነ ደረጃ ደካማ ነበር ነው ያሉት።

በመጨረሻም ነገሮችን ለመለወጥ አሁንም ጊዜ አለን ሲሉም ሪክ ሄልፌንቤይን ባሰፈሩት ሃሳብ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.