Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በትብብር የምታካሂደውን ፀረ ሽብር ዘመቻ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ  ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በትብብር እያካሄደች ያለውን ፀረ ሽብር ዘመቻ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናገረች።

የአሜሪካ የአፍሪካ ልዩ ዘመቻ ዋና አዛዠ ሜጀር ጀኔራል ዳቪገን አንደርሰን የኮሮና ቫይርስ ወረርሽኝ እና ፀረ ሽብር ዘመቻ እንቅስቃሴ ዙርያ በአፍሪካ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን  ለሚሰሩ ጋዜጠኞች በኢንተርኔት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሜጀር ጀኔራል አንደርሰን በዚህ ማብራሪያቸውም፥ በአፍሪካ የሚካሄደውን ፀረ ሽብር ዘመቻ  አሸባሪዎች እና ፀንፈኞች እስካልጠፉ ድረስ ምንም አይነት ሃይል አያስቆመውም ነው ያሉት።

በምስራቅ አፍሪካ  በአሸባሪው አል ሽባብ እና ሌሎች የሽብር ቡድኖች ላይ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ አሁን ላይ በምን ደረጃ ይገኛል በሚል ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለቀረበላቸው ጥያቄም ዋና አዛዡ ሜጀር ጀኔራል አንደርሰን ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም በምስራቅ አፍሪካ በሚካሄደው ፀረ ሽብር ዘመቻ አሜሪካ ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ እና ከአሚሶም ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር የሽብር ቡድኑ እስኪከስም ድረስ ትገፋበታለች ነው ያሉት።

በሶማሊያ እየተንቀሳቀሰ ያለው አሸባሪው አልሸባብ ሙሉ በሙሉ ካልተደመሰሰ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዳይፈጠር ያደርጋል ብለዋል።

ሜጀር ጀኔራል ዳቪገን አንደርሰን አክልውም አሜሪካ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር እንዲጠናከር ከማገዝ በተጨማሪ የቀጣናው ሀገራት የሚያደርጉትን ፀረ ሽበር ዘመቻ ይበልጥ እንዲጠናከርም ድጋፏን ትቸራለች ነው ያሉት።

በስላባት ማናዬ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.