Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ እስከ ፈረንጆቹ 2030 ከምታመርታቸው መኪኖች ግማሽ ያህሉ የካርቦን ልቀት የሌላቸው እንደሚሆኑ ገለፀች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እስከ ፈረንጆቹ 2030 ከምታመርታቸው መኪኖች ግማሽ ያህሉ የካርቦን ልቀት የሌላቸው እንደሚሆኑ ገለፀች፡፡

እቅዱ የሚሳካ ከሆነም በከባቢ አየር ላይ የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ በመቀነስ ረገድ ከቻይና ጋር መወዳደር ያስችላታል ነው የተባለው፡፡

በፈረንጆቹ 2019 ከሀገሪቷ የትራንስፖርት ዘርፍ የተለቀቀው የካርቦን መጠን 29 በመቶ ለሚሆነውን ብክለት መንስኤ እንደነበረም ነው የተገለፀው፡፡

ከቻይናና አውሮፓ አንፃር በአሜሪካ የካርበን ልቀት መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ መኪኖች ሽያጭ ዝቅተኛ እንደነበረም ነው የተመለከተው፡፡

ይህን ተከትሎ ሦሥት ግዙፍ የአሜሪካ መኪና አምራች ኩባንያዎች የመንግስትን ዕቅድ ለማሳካት እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡

ከኢንዱስትሪ አብዮት ወዲህ የዓለም የሙቀት መጠን በ 1 ነጥብ 2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እንደጨመረና ሀገራት ከከባቢ አየር ጋር ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት መጠቀም ካልጀመሩ ሙቀት መጨመሩን እንደሚቀጥል ነው በመረጃው የተመላከተው፡፡

የአካባቢ ጥበቃ እና የካርበን ልቀት መጠን ቁጥጥር ቀደም ሲል በአሜሪካ ችላ ተብሎ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ አሁን ግን አሜሪካ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥታ የወጡ ደንቦችን ባከበረ መልኩ እንደምትሰራ ነው የገለፀችው፡፡

ምንጭ÷ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.