Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከብራዚል የሚመጡ መንገደኞች እንዳይገቡ እግድ ጣለች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋሽንግተን ከብራዚል ወደ አሜሪካ በሚገቡ የውጭ ሃገር ተጓዞች ላይ እገዳ ጣለች።

እገዳው የአሜሪካ ዜጎችን የማይመለከት ሲሆን ላለፉት 14 ቀናት በብራዚል ቆይተው ወደ አሜሪካ በሚገቡ የውጭ ሃገር ተጓዦች ላይ የተጣለ ነው ተብሏል።

የአሁኑ እገዳ ኮሮና ቫይረስ በብራዚል በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱን ተከትሎ የተጣለ ነው።

ዋሽንግተን ከዚህ ቀደም ኢራንን ጨምሮ ከአውሮፓ ሕብረት አባል ሃገራት ወደ አሜሪካ የሚመጡ መንገደኞች እንዳይገቡባት እግድ መጣሏ ይታወሳል።

የኮሮና ቫይረስ በብራዚል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋ ሲሆን፥ ብራዚል ቫይረሱ በተገኘባቸው ሰዎች ብዛት ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

በቫይረሱ ሳቢያም እስካሁን ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.