Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባት መሥጠት ልትጀምር መሆኑን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 300 ያህል አሜሪካውያን በዝንጀሮ ፈንጣጣ መጠቃታቸውን ተከትሎ ሀገሪቱ በተለያዩ ግዛቶቿ ክትባት መስጠት ልትጀምር ነው።

በመጪዎቹ ወራት 300 ሺህ ያህል ክትባቶችን ለማሰራጨትም ዋይት ሀውስ ያዘጋጀው ዕቅድ ያመለክታል።

በሚቀጥለው ዓመት 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ያህል ክትባቶች እንደሚያሰራጩም ነው የተጠቆመው፡፡

አሜሪካ ክትባት የማሠራጨቱን ዕቅድ ተግባራዊ ስታደርግ የቫይረሱን ሥርጭት በፍጥነት መግታት እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

የክትባት ሥርጭት ዕቅድ የመጀመሪያ የትግበራ ምዕራፍ የሚሆኑትም በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰቦች ክፍሎች መሆናቸውም ነው የተነገረው፡፡

እስካሁን 32 የአሜሪካ ግዛቶች እና አስተዳደሮች ክትባቱን ለማግኘት ጠይቀዋል።

የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) እስከ ትናንት ድረስ በአጠቃላይ በአሜሪካ ውስጥ 305 ዜጎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዛቸውን አረጋግጧል።

በቀጣይም የሚካሄደው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ልየታ ምርመራ ወደ ሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች እንደሚሰፋና በማዕከሉ በኩል ክትባት እንደሚሰራጭም መገለጹን አር ቲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.