Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶዝ በላይ ተጨማሪ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶዝ በላይ ተጨማሪ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ አድርጋለች፡፡
 
ድጋፉን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ለጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ አስረክበዋል፡፡
 
 
በአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ ድጋፍ የተደረገው ክትባት “ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን” የተሰኘው ክትባት መሆኑን አምባሳደር ጊታ ፓሲ ተናግረዋል፡፡
 
የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፍም ኢትዮጵያ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑንም መናገራቸውን ከኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.