Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የልምምድና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቀሶችን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሜሪካ 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የልምምድና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቀሶችን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጓን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ።
 
ይህ ድጋፍ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ቡድን እና ሌሎች የሽብር ድርጅቶችን ሊፈጥሩት የሚችሉትን አደጋዎች ለመመከት የሚያግዘው መሆኑ ተጠቁሟል።
 
የአሜሪካ መከለከያ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የገለፀው ኤምባሲው በተያዘው ዓመት የተደረገው ድጋፍም የዚሁ አካል ነው ተብሏል።
 
ድጋፉም አምቡላንስ ፣ ላንድ ክሮዘር ፣የእቃና የነዳጅ መጫኛ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም የምሽት አጉሊ መነፀር እንደሚያካትት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ሽብርተኝነትን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የተደረገ አንደኛው የድጋፍ አይነት ነው ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.