Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በአውሮፓ ህብረት ከጀርመንና ፈረንሳይ ቋሚ መልዕክተኞች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም ብራሰልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በአውሮፓ ህብረት ከጀርመንና ፈረንሳይ ቋሚ መልዕክተኞች ጋር መከሩ፡፡

አምባሳደር ሂሩት ከህብረቱ የፖለቲካና ደህንነት ቋሚ ኮሚቴ አባላት አምባሳደር ቶማስ ኦሶውስኪ እና አምባሳደር ክሌይር ሩዋሊን ጋር መክረዋል፡፡

ባካሄዱት የቪዲዮ ውይይትም የኢትዮጵያን እና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ሂሩት ኢትዮጵያ እያካሄደች ስላለችው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያንና የአውሮፓ ህብረትን መልካም ግንኙነት ማጠናከር አስፈላጊ ስለመሆኑም በምክክራቸው ወቅት አንስተዋል፡፡

አምባሳደሯ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.