Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከእስራኤል የትራንስፖርትና የመንገድ ደህንነት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከእስራኤል የትራንስፖርትና የመንገድ ደህንነት ሚኒስትር ሚሪ ሬጌቭ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ በትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡
በውይይቱ የእስራኤል ምክትል የደህንነት ሚኒስትር አቶ ጋዲ ይባርከኝ በሁለቱ ሃገራት መካከል ትብብሩ እንዲጠናከር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሁለቱ ወገኖች የአየር ትራንስፖርት ትብብር ማዕቀፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንቅስቃሴ እንዲጠናከር መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከእስራዔል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.