Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ብርቱካን ሀብት የማፍራት ስራን በተመለከተ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት ከወከሉ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት ከወከሉ አምባሳደሮች ጋር ሀብት የማፍራት ስራን በተመለከተ በበይነ መረብ ተወያይተዋል።
ውይይቱ ጂቡቲ፣ ናይሮቢ እና ዳካር ከሚገኙ አምባሳደሮች ጋር የተደረገ ነው።
ውይይቱ በውጭ ሀገራት ያሉ ሚሲዮኖች ሀብት በማፍራት የተሳለጠ የዲፕሎማሲያዊ ሥራ ማከናወን እና ሀገሪቱ በመደጋገፍ መርህ የምታገኛቸውን ጥቅሞች አሟጦ ለመጠቀም በተያዙ ሥራዎች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም በዳካር እየተገነባ ያለው የአምባሳደር መኖሪያ ግንባታ ሂደት፣ በጂቡቲ እየተገነባ ያለው የአምባሳደር መኖሪያና የዲፕሎማቶች መኖሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ እድሳት እንዲሁም በናይሮቢ ለኤምባሲው ለሚገነባው ቢሮና የቢዝነስ ህንፃ ግንባታ ዝግጅት ተገምግሟል።
ሚኒስትር ዲኤታዋ ሀብት ለማሰባሰብና በቀጣይ ሥራውን ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለአምባሳደሮች አቅጣጫ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.