Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በኢንዲያና ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ስለ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በኢንዲያና ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ስለ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጡ።

ምክር ቤቱ በአለማቀፍ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ባዘጋጀው ውይይት ላይ አምባሳደር ታዬ በኢትዮጵያ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬቶችና ተግዳሮቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና ቀጠናዊ ትብብር ላይም ሀሳባቸውን አካፍለዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ስላላት ሁለንተናዊ ሚናም አብራርተዋል።

አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው እንዳሳወቁት የኢትዮጵያን ህልውናና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የህግ ማስከበር ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

ሰብዓዊ ድጋፍን ማቅረብና መሰረተልማቶችን መልሶ መገንባት ላይ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎችም ገለጻ አድርገዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.