Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከቻይና አምባሳደር ማ ዚንሚንጋር በወቅታዊ ሃገራዊና ቀጠናው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅት አምባሳደር ይበልጣል በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ እየተደረገ ስላለው ዝግጅት፣ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል፡፡

የቻይናው አቻቸው ማ ዚንሚን በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይዋን በራሷ መንገድ ያለማንም ጣልቃ ገብነት መፍታት መብቷ እንደሆነ ገልጸዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይን እና የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ በድርድር እና ሠላማዊ መንገድ ሊፈታ እንደሚገባ የሀገራቸው አቋም እንደሆነ ተናግረዋል።

አያይዘውም ሀገራቸው የአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሶስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.