Fana: At a Speed of Life!

አራተኛው ሀገር አቀፍ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በነገው ዕለት በድሬዳዋ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አራተኛው ሀገር አቀፍ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን “ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን” በሚል መሪ ቃል በነገው ዕለት በድሬዳዋ ይካሄዳል።

ቀኑ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በተገኙበት እንደሚካሄድ ከአስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ፖርክ፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ሬድዋ ሞተርስ የቲቪኤስና የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም አዲሱን መናኸሪያ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አህመድ ቡህ፣ የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የካቢኔ አባላት ተገኝተዋል።

ሀገር አቀፍ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞችም በተመሳሳይ ቀን እንደሚካሄድ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀቱን በመጠበቅና አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በየአካባቢው እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርቧል።

ሁነቱ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን ከማስተዋወቁም በላይ ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ ያስችላል ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.