Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ።

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በጤና፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በትምህርትና ስነባህሪ፣ በህግ፣ በማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስና በግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጆች ያሰለጠናቸው 1 ሺህ 959 ተማሪዎቹን ነው ያስመረቀው።

ከተመራቂዎች መካከል 732ቱ ሴቶች ናቸው።

በተመሳሳይ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመጀሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 229 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በመጀመሪያ ዲግሪ 958 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከነዚህም 389 ሴቶች፥ 596 ደግሞ ወንዶች ናቸው።

በሁለተኛ ዲግሪ 45 ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን ከነዚህ መካከል አምስቱ ሴቶች ናቸው።

መቱ ዩኒቨርሲቲ በደሌ ካምፓስም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 543 ተማሪዎችን አርመርቋል።

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስም 805 ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲው 2ሺህ 127 ተማሪዎችን በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች አስመርቋል።

ከእነዚህ ተመራቂዎች ውስጥ 666 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.