Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደሩ የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ እንዲተገብሩ አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

አስተዳደሩ በከተማዋ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎች ትርፍ መጫን የተከለከለ መሆኑን እንዲሁም አውቶብሶች በወንበር ልክ ብቻ እንዲጭኑ መወሰኑን አስታውሷል።

ይሁን እንጅ በተለይም የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎች ትርፍ እየጫኑ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን መረጃዎች እንደደረሱት አስታውቋል።

ስለሆነም በታክሲዎችና በባጃጆች በኩል የሚታየው ትርፍ የመጫን ሁኔታ በኃላፊነት ስሜት በፍጥነት መስተካከል ካልቻለ ለዜጎች ደህንነት ሲባል ታክሲዎችንና ባጃጆችን ከስራ ውጭ ለማድረግ እንደሚገደድም ገልጿል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ጤንነት ለመጠበቅ ሲባል ያወጣቸውን መመሪያዎች እንዲያከብሩና የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡም ጥሪውን አቅርቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.