Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪውን የሸኔ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከህዝባችን ጋር እናስወግደዋለን – ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “አሸባሪውን የሸኔ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከህዝባችን ጋር እናስወግደዋለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው  ባሰራጩት መልዕክት፥ የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች በሽብር ቡድኑ  ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል ነው ያሉት።

“በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን፥ ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከህዝባችን ጋር እናስወግደዋለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.