Fana: At a Speed of Life!

“አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ከምድረ ገፅ ማጥፋት አለብን” ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአሸባሪው ትህነግ ተቀዳሚ ዓላማ ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑን ገለጹ፡፡

አሸባሪው ትህነግ በአማራና አፋር ክልል ጦርነት በመጀመር ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሊያጠቃ ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአሸባሪው ቡድን ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ ሴራ በመረዳት በህልውና ዘመቻው ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፥ “አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ከምድረ ገፅ ማጥፋት አለብን” ነው ያሉት፡፡

የአሸባሪ ቡድኑን የሐሰት ፕሮፓጋንዳና አሉባልታ የሚያናፍሱ በሕዝብ ውስጥ ያሉ ተላላኪዎችን ማኅበረሰቡ በንቃት ሊከታተል ይገባልም ብለዋል ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ።

መንግሥት ያስተላለፈውን ጥሪ ተቀብሎ ሕዝቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፥ ትግሉን ወጣቱ በጉልበቱ፣ ሕዝቡና ባለሃብቱ በሎጅስቲክ ሊያግዙ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው የጠየቁት፡፡

የጦር ልምድ ያላቸው መሪዎችና ተዋጊዎች ወደ ልዩ ኃይል እየተቀላቀሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የትግራይ ሕዝብ ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራሉ ዛሬ እየሆነ ያለው ጊዜያዊ ነው፤ ዘላቂ ወንድሙ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ብለዋል።

አሸባሪው ትህነግ ሕጻናትን ወደ እሳት እየማገደ መሆኑን የገለጹት አዛዡ የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን ከዚህ ውድመት ማዳን እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአማራ ልዩ ኃይል ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር እየተናበበ በቅንጅት እየተዋጋ ስለመሆኑም አስታውቀዋል።

ለኢትዮጵያ ዘብ ቆመው አሸባሪውን ቡድን በግንባር በመፋለም ላይ ላሉ የጸጥታ ኃይሎች ምስጋና ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.