Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በአማራና አፋር ክልሎች የሚያደርገውን ትንኮሳ አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች የሚያደርገውን ትንኮሳ አጠናክሮ መቀጠሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የዓለም አቀፍ ግንኙትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ቢለኔ ስዩም በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ኃላፊዋ በመግለጫቸው አሸባሪው ትህነግ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚያደርገውን ትንኮሳ ተከትሎ የዜጎች መፈናቀል ችግር እየተባባሰ መሄዱን ተናግረዋል፡፡

በአንፃሩ መንግሥት አሁንም የተኩስ አቁም ውሳኔውን እንዳከበረ መሆኑንም ገልጸዋል።

ወደ ትግራይ ክልል የሚገባው የሰብዓዊ እርዳታ በፍጥነት ለተጎጂዎች እንዲደርስ መንግስት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን አሁንም ሀሰተኛ መረጃዎችን በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ በማስተላለፍ ሰዎችን የማደናገር ሥራ ውስጥ መግባቱን ጠቁመዋል።

ከእነዚህም መካከል በማኅበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚተላለፈው “መንግሥት በትግራይ ሕዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ዘመቻ ጀምሯል” የሚለው አንዱ መሆኑን ገልጸው÷ ይህም የሃሰት ዘመቻው አካል መሆኑን አስረድተዋል።

በተመሳሳይ “በሁመራ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ተፈጽሟል” የሚል የሀሰት ዘመቻ ሲያካሄድ መቆየቱን ጠቁመው÷ ይህም የቡድኑ ቅጥረኞች የሚያካሂዱት መሆኑን ገልጸዋል።

አሸባሪው ቡድን በአፋር በኩል ጥቃት እየፈጸመ በጎን ደግሞ “መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተላለፊያ ዘግቷል” ብሎ እየተናገረ መሆኑን ነው የጠቆሙት።

ይህም ቡድኑ ሌላ ተጨማሪ መተላላለፊያ ኮሪደር እንዲከፈት በማሰብ የሚሰራበት እቅድ መሆኑን መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ያለቡድኑ ከሰብዓዊ ድጋፍ ውጪ መሳሪያና ሌሎች ድጋፍ እንዲቀርብላቸው የሚፈልጉ አካላት ሌላ መስመር እንዲከፈት ግፊት እያደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.