Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በአፋር አባላ እየፈፀመ ያለውን ጥቃት እንዲያቆም የብሪታኒያ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአፋር አባላ በኩል እየፈፀመ ያለውን ጥቃት እንዲያቆም በብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ አሳሰቡ፡፡

ረዳት ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ በአባላ በኩል ህወሓት የከፈተው ጥቃት ወደ ትግራይ ክልል የሚገባውን የሰብዓዊ እርዳታ እያደናቀፈ መሆኑን ገልፀዋል።

ቪኪ ፎርድ ህወሓት ድርጊቱን ማቆም አለበት፤ ሰላማዊ ህዝብ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባልም ብለዋል።

የባልሲሊ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤት እና የዊልፍሬድ ላውሪየር ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካል ሣይንስ የትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጀራልድ፥ የረዳት ሚኒስትሯን ጥሪ ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት አስተያየት የቪኪ ፎርድን መንገድ ሌሎች ህወሓትን በተመለከተ ዓይናቸውን ሸብበው የተቀመጡ ሀገራትም ሊከተሉ ይገባል ብለዋል።

አን ፊትዝ ጀራልድ ህወሓት በአውሮፓውያኑ 1980ዎቹ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በአባላ በኩል ጥቃት በመክፈት እና የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይገባ በመከልከል “ተከበናል”እና “ተከልክለናል” ለሚለው ጩኸቱ ማሳመኛ እየፈለገ ነው ይላሉ።

ቡድኑ በአባላ በኩል ጥቃት መክፈቱ ጦርነቱን የማቆም ፍላጎት እንደለሌው ማሳያም እንደሆነም አስረደተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.