Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በደብረሲና ከተማ የህክምና ተቋማትን ሙሉ በሙሉ አውድሟል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በደብረሲና ከተማ ያሉ ጤና ጣቢያዎችንና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ተገለጸ።
ቡድኑ ከተቋማቱ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን ዘርፏል፤ መውሰድ ያልቻለውን ደግሞ ለአገልግሎት እንዳይውል አድርጓል፡፡
የጣርማበር ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድም ተሰማ እንደተናገሩት÷ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የተሟላ ግብዓት ነበረው።
ይሁን እንጂ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በወረዳው ያሉ አራት ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ሙሉ በሙሉ አውድሟል።
በጤና ተቋሞች የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ፣ የላቦራቶሪ እቃዎች፣ መድሀኒቶች በሙሉ ተዘርፈዋል፣ ቀሪዎቹን ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል ነው ያሉት፡፡
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሁሉም የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉም ነው የገለጹት፡፡
በዚህም ከእነርሱ ጥይት የተረፈውን በህክምና እጦት እንዲሞት በማድረግ ለህዝብ ያላቸውን ጥላቻ በተግባር አሳይተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.