Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት የጅምላ ግድያ ፈጽሟል – ቢለኔ ስዩም

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የጅምላ ግድያ መፈጸሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የዓለም አቀፍ ግንኙትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ቢለኔ ስዩም ገለጹ።
 
ኃላፊዋ ለውጭ አገር መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ህወሓት በሁለቱ ክልሎች ወረራ በመፈጸም ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን ገልጸዋል።
 
በተለይም በአማራ ክልል አንጾኪያ እና ጋሸና የጅምላ መቃብር መገኘቱን አስረድተዋል።
 
ከዚህ ባለፈም በአማራ እና አፋር ክልሎች በንጹሃን ላይ ግድያ መፈጸሙን የጠቀሱት ኃላፊዋ፥ ሴቶችን መድፈሩን እና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማድረሱንም ነው በመግለጫቸው ያነሱት።
 
ቡድኑ በሁለቱ ክልሎች በፈጸመው ወረራ በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለከፋ ችግር መዳረጋቸውንም ነው ያስረዱት።
 
ከዚህ በተጨማሪም ህወሓት ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጨምሮ በመሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል ነው ያሉት።
 
ይሁን እንጅ ምዕራባውያን ዝምታን መምረጣቸውን ጠቁመው፥ የሽብር ቡድኑ የፈጸመውን ወንጀል ማጋለጥ እና ቡድኑን በሰብዓዊ መብት ወንጀል እንዲጠየቅ መስራት አለባቸው ብለዋል።
 
ቢለኔ በማብራሪያቸው አሸባሪ ቡድኑ እየተደመሰሰ እና ታጣቂዎቹም የቀረበውን አማራጭ በመጠቀም እጅ እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ከዚህ በተጓዳኝም መንግስት አሁን ላይ ለተፈናቃይ ወገኖች የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
 
በአለማየሁ ገረመው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.