Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ሸኔ እና የጥፋት አጋሮቹ በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ጥቃት የፈጸሙት ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ሸኔ እና የጥፋት አጋሮቹ በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ጥቃት የፈጸሙት ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት አስበው መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

የክልሉ መንግስት አሸባሪውን ሸኔ በዘላቂነት ለማጥፋት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ጌታቸው ኢታና መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም አሸባሪው ሸኔ እና የጥፋት አጋሮቹ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ሆራ አዲስ የተባለች የገጠር ከተማ ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ጥቃት የፈጸሙትን የአሸባሪው ሸኔ አባላትን ለመደምሰስና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

ረዳት ኮሚሽነር ጌታቸው እንደገለጹት ፥ በዕለቱ ጸረ ሰላም ሀይሎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ብሔርን ከብሔር በማጋጨት አልመው ነው።

የጥፋት ሀይሎቹ ላይ በተወሰደው እርምጃም የአሸባሪው ሸኔ አባላት ተገድለዋል።

በአሁኑ ወቅት የተፈናቀሉት ዜጎችም በኪረሙ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸው ፥ ተፈናቃዮቹን ወደ ነበሩበት አካባቢ ለመመለስም እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

የክልሉ መንግስት አሸባሪው ሸኔ በዘላቂነት ለማጥፋት የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

እንደ ረዳት ኮሚሸነሩ ገለጻ፤ በምስራቅ ወለጋና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ በሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ቡድን ላይ ጠንካራ እርምጃም ይወሰዳል።

በሌላ በኩል የተወሰኑ መገናኛ ብዙሃን የጉዳቱ ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ብሔር አባላት ሆነው ሳለ ተጎጂዎችን የአንድ ብሔር አባላት ማድረጉ ተገቢ እንዳልሆነም ጠቅሰዋል።

በቀጣይም መገናኛ ብዙሃን ትክክለኛውን መረጃ ከተገቢ አካላት ማጣራት እንደሚኖርባቸውም ጠቁመዋል።

በአካባቢው የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ሁሉ መሰዋዕትነት እየከፈሉ እንደሚገኙም  መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.