Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ትህነግ የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ስብስብ ነው-አቶ ጌታቸው ባልቻ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ትህነግ የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ስብስብ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገለጹ።
የአሸባሪው ትህነግ ስብስብ የመንግስትን ተናጠላዊ የተኩስ አቁም ውሳኔን ያልተቀበለ፣ በተፈጥሮው ሰላም የማይፈልግና የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ አስታወቁ።
የአዳማ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል።
አቶ ጌታቸው ባልቻ በአዳማ ከተማ የተካሄደውን የህዝቡን የድጋፍ ሰልፍ አስመልክተው ትናንት እንደገለፁት÷ የአሸባሪው ጁንታ ትህነግ ስብስብ በተፈጥሮው ሰላም የማይፈልግና የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በአዳማ ከተማ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የኦሮሞ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ለመከላከያው ድጋፍ ማድረግ አለብን በማለት እየተደረጉ ካሉ ድጋፎች ውስጥ አንዱ ነው ያሉት አቶ ጌታቸው÷ አሸባሪው ጁንታ እየፈፀመ ያለው የኢትዮጵያ ህዝቦችን የማይወክል ሀገር ለማፍረስ የሚደረግ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ለመከላከያው ድጋፉን እየገለፀ የአሻባሪውን ድርጊት በማውገዝ ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.