Fana: At a Speed of Life!

አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አቅርቦ ጭብጥ አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብ  በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ  የሚመሰክሩ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን  አቅርቦ ጭብጥ አስመዘገበ።

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪዎቹ የቀረቡ ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ በ3ኛ፣ 13ኛ እና 14ኛ ተጠርጣሪዎች  በድጋሜ የኮቪድ-19 ምርመራ  እንዲደረግላቸው  ያቀረቡትን  አቤቱታ ተከትሎ የአዲስ አበባ እስረኞች አስተዳደር ተወካይ  በባለፈው  ቀርቦ አለማብራራቱን ተከትሎ ታስሮ እንዲቀርብ በሰጠው ትእዛዝ  መሰረት ቀርቧል።

ተወካዩ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ እስረኞች መሆናቸውን  ጠቅሶ  በውሰት አዲስ አበባ  ፖሊስ ኮሚሽን  መቆየታቸውን  ይሁን እንጂ  በዚያው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኮቪድ ምርመራ እንደተደረገላቸው ማብራሪያ ሰጥቷል።

ከዚህ በፊት ለምን አልቀረብክም ተብሎ በፍርድ ቤቱ ለቀረበለት ጥያቄ  ተእዛዝ እንዳልደረሰው ገልጿል።

ፍርድ ቤቱም እነዚህ ተጠርጣሪዎች በድጋሚ  የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጥቷል።

ይህ ካልተፈፀመ ፍርድ ቤቱ እንደሚቀጣው አፅንኦት ሰጥቷል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማቅረቡን ገልፆ የምስክሮችን ስም አስመዝግቧል።

በዚህም መሰረትም አቃቤ ህግ ተጨማሪ አራት ምስክሮችን አሰምቷል።

ይሁን እና ፍርድ ቤቱ አራተኛዋ ምስክር ላይ የተጀመረው የመስቀለኛ እና የማጣሪያ ጥያቄ ስላላለቀ በይደር ምስክሯ ቀርበው መስቀለኛ እና ማጣሪያ ጥያቄው እንዲቀርብላቸውና ሌላ ቀሩ የአቃቤ ህግ ቅድመ ምርመራ ምስክርን ለመስማት በይደር ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በአጠቃላይ አቃቤ ህግ እስከለ ዛሬ ድረስ ሰባት የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰምቷል።

ዛሬ ተጠርጣሪዎቹ ከ7 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ከ30 የነበረው የምሳ ሰዓት እረፍት ምግብ አለመመገባቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ቀ2ጣይ ምስርሮቹ ሙሉ ቀን ስለሚሰሙ ምምሳ ሰዓት ምገብ የሚመገቡበት ሁኔታ ፖሊስ ያመቻችላቸው ብሏል።

የዛሬው የምስክሮች ቃል ተገልብጦ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ አዟል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.