Fana: At a Speed of Life!

አባቶቻችን በደምና በአጥንት ያስረከቡንን ሀገር ከነክብሯ ጠብቀን ለቀጣዮ ትውልድ እናስተላልፍለን-የደሴ ከተማ ወጣቶች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አባቶቻችን በደምና በአጥንት ያስረከቡንን ሀገር ከነክብሯ ጠብቀን ለቀጣዮ ትውልድ እናስተላልፍለን ሲሉ የደሴ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።
ወጣቶቹ ሀገራችን የገጠማትን የህልውና አደጋ ለመመከትና የጸጥታ ሀይሉን ለመቀላቀል በየአካባቢያቸው መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።
በስልጠናው ላይ ያገኛናቸው ወጣቶች ለጣቢያችን እንደተናገሩት ÷ ኢትዮጵያ ጠላቶቿ እንደሚሉት የምትፈርስ ሳትሆን በልጆቿ ተከብራ የምትቀጥል ሀገር ናት ብለዋል።
ኢትዮጵያን ለማሻገር እስከ ግንባር ድረስ በማቅናት መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውንም ወጣቶቹ ተናግረዋል።
ጁንታውና መሠሎችን ጠራርጎ ለማጥፍት ግዜው አሁን ነው ያሉት ወጣቶቹ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ዝግጁ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በስልጠናው ወቅት ያገኘናቸው የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል በበኩላቸው ÷በከተማዋ በሁሉም አቅጣጫ ለወጣቶች መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና እየተሠጠ ነው ብለዋል።
ስልጠናው ሀገር ለማፍረስ እየሠራ ያለውን የወያኔ አሸባሪ ቡድን ሴራ ለማክሸፍ የሚደረግ ዝግጅት ነው ያሉት።
ከንቲባው ወጣቱ ትውልድ አባቶቹ ያቆዩለትን ሀገር ለማስቀጠልና ሀገርን ከጥፍት ለመታደግ በያለበት ዝግጅት ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.