Fana: At a Speed of Life!

አብራሪዎች እና የበረራ አስተናጋጆች በመዲናዋ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች እና የበረራ አስተናጋጆች በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

አብራሪዎቹ እና የበረራ አስተናጋጆቹ እየተገነቡ ካሉት ፕሮጀክቶች ውስጥ የእንጦጦ እና የሸገር ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም አዲስ አበባን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰሩ ስላሉ የልማት ስራዎች ለአብራሪዎችና የበረራ አስተናጋጆቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አብራሪዎቹና የበረራ አስተናጋጆቹም የከተማ አስተዳደሩ እየሰራቸው ባሉ ማህበራዊ ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.