Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ሃጎስ በጣልያን በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጣልያን በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ሃጎስ ገብረህይወት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸናፊ ሆኗል፡፡
አትሌት ሃጎስ ርቀቱን 29 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸንፏል፡፡
የቀድሞው የቦታው ክብረ ወሰን 30 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ እንደነበር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በሌላ ዜና በጊዲኒያ በተካሄደው የዓለም ግማሽ ማራቶን የተሳተፈውና ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።
ቡድኑ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።
ለቡድኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ አቀባበል አድርገውለታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.