Fana: At a Speed of Life!

አትሌት አባብል የሻነህ በግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ራስ አል ከሂማህ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች።

አትሌት አባብል በፈረንጆቹ 2017 ኬንያዊቷ አትሌት ጆይስሊን ጄፕኮስጊ በቫሌንሺያ የያዘችውን ክብረ ወሰን በ20 ሰከንድ በማሻሻል አሸንፋለች።

በውድድሩ አትሌት አባብል የሻነህ ርቀቱን 1 ሰዓት፣ ከ4 ደቂቃ፣ ከ31 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች።

በውድድሩ ኬንያውያን አትሌቶች ከ2 እስከ 5 ያለውን ደረጃ ይዘው ተከታትለው ሲገቡ፥ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ ጥላሁን 6ኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን አጠናቃለች።

በወንዶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ አትሌት ሙሌ ዋስይሁን 59 ደቂቃ፣ ከ47 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

ውድድሩን ኬንያውያኑ ኪብዎት ካንዲይ እና አሌክሳንደር ሙቲሱ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን የአፍሪካ አትሌቲክስ ዩናይትድ መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.