Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ዳዊት ስዩም የ5 ኪሎ ሜትር ሚክስድ ሬስ የዓለም ሪከርድ ሰበረች

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ)በፈረንሳይ ሊል በተደረገ የ5 ኪሎ ሜትር የድብልቅ ውድድር (ሚክስ ሬስ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዳዊት ስዩም የርቀቱን የዓለም ሪከርድ በመስበር አሸንፋለች።

አትሌቷ በ14:41 በመግባት ነው የርቀቱን የዓለም ሪከርድ በመስበር አሸናፊ መሆን የቻለችው፡፡

በተጨማሪም አትሌት መስከረም ማሞ በ14:55 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

በወንዶቹ ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ12:52 በሆነ ሰዓት ሲያሸንፍ ሌላው አትሌት ያሲን ሃጂ በ13:29 በሆነ ሰዓት 3ኛ ወጥቷል።

በሌላ በኩል በ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ በ27:16 በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ማሞ አደላድለው በ27:27 በመግባት ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.