Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ሚዛን አለም ለኢትዮጵያ ሦስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በመጨረሻው ቀን ኢትዮጵያን የወከሉ አትሌቶች በተለያየ መርሃግብር ተሳትፈዋል፡፡
በ5000 ሜትር ሴቶች ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ሚዛን አለም በ16:05.61 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ያገኘችው የወርቅ ሜዳልያ ቁጥርም ሶስት ደርሷል፡፡

በሌላ ውድድር በ1500 ሜትር ሴቶች ድርቤ ወልተጂ እና ታደሰ ታከለ በ3000 ሜትር መሠናክል 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስመዝግበዋል፡፡

አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ 4:16.39 በሆነ ሰዓት በመግባት ነው የብር ሜዳልያ ያስገኘችው፡፡
በዚሁ ውድድር አትሌት ህይወት መሀሪ በ 4:23.23 በሆነ ሰዓት 4ኛ ደረጃ ይዛ በማጠናቀቅ ዲፕሎማ አግኝታለች፡፡
በሌላ መርሃ ግብር በ3000 ሜትር መሠናክል ወንዶች አትሌት ታደሰ ታከለ በ8:33.15 በሆነ ሰዓት 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡
አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ደግሞ በ8:46.16 በሆነ ሰዓት 4ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ ዲፕሎማ አግኝቷል፡፡
ፍፃሜውን ባገኘው የ800 ሜትር ወንዶች ውድድር አትሌት ዳንኤል ወልዴ በ1:48.62 በሆነ ሰአት 5ኛ በመውጣት ዲፕሎማ ማግኘቱን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.