Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የ”ኢምፓክት አዋርድ” ተሸላሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በአሜሪካ የሚገኘው ኖቫ ኮኔክሽንስ የሚያዘጋጀው “ኢምፓክት አዋርድ” ተሸላሚ ሆነች።

አትሌቷ በአትሌቲክስ ዘርፍ በተደጋጋሚ ባስመዘገበቻቸው አስደናቂ ውጤቶች እና በዓለም ላይ ለሚገኙ ታዳጊዎች ትልቅ የስኬት ተምሳሌት በመሆኗ ነው ተሸላሚ የሆነችው ተብሏል።

ሌላው ተሸላሚ አቶ በረከት ወልዱ በዋሽንግተን ዲ.ሲ. እና አካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ብሎም የሌሎች አፍሪካ አገሮች ዳያስፖራዎች የስራ ዕድልና የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ ድጋፍ በማድረጋቸው ተሸላሚ ሆነዋል።

በሙዚቃው የባህል ልውውጥ በማድረግ መቀራረብ እንዲፈጠር ብሎም ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም በአፍሪካ በሚያደርገው የበጎ አድራጎት ስራ የሴኔጋሉ ሙዚቀኛ ኤኮን ቲያም ተሸልሟል፡፡

በዝግጅቱ ላይ በአሜሪካ የአፍሪካ ህብረት አምባሳደር፣ የአሜሪካ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የኢምፓክት የመጀመሪያ ተሸላሚ አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ም/ፕሬዚዳንት አትሌት ብርሃኔ አደሬ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ ስለሺ ስህን፣ ሚሊዮን ወልዴ፣ ቁጥሬ ዱለቻ እና ሌሎችም የቀድሞ አትሌቶች እና ተጋባዥ እንግዶች መገኘታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

የአትሌት ጥሩ ነሽ ዲባባ ሽልማትን እህቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የተቀበለች ሲሆን  የሙዚቀኛ ኤኮንን ኢትዮጵያዊት ባለቤቱ ሮዚና  ንጉሴ ተቀብላለታለች፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.