Fana: At a Speed of Life!

አትሌቷ የ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር እና 40 ግራም የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበረከተላት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በቶኪዮ 2020 ፖራሊምፒክ ጨዋታ የተሳተፉ የልዑካን አባላት የእውቅናና የማበረታቻ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በቶኪዮ 2020 ፖራሊምፒክ ጨዋታ በ1500 ሜትር T-13 አይነስውራን ጭላንጭል ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ የ2ነጥብ 8 ሚሊየን ብር እና 40 ግራም የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል።

አትሌቷ 04:23:24 በሆነ ሰዓት በመግባት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ በማስመዝገብ በፖራሊምፒክ ጨዋታ ታሪክ መስራቷ ይታወሳል።

የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ንጋቱ ኃ/ማሪያም 400 ሺህ ብር ተሸልሟል።

በ1500 ሜትር እጅ ጉዳት T-46 5ኛ ደረጃን በመያዝ ዲፕሎማ ያስመዘገበው አትሌት ገመቹ አመኑ የ200ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

በተመሳሳይ በ1500 ሜትር አይነስውራን ጭላንጭል T-13 7ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው አትሌት ታምሩ ከፍያለው 150 ሺህ ብር ተሸልሟል።

በተጨማሪም የቡድኑ ሀኪም 100 ሺህ ብር ተሸልሟል።

በቶኪዮ 2020 ፖራሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሶስት አትሌቶች የተወከለች ሲሆን÷አንድ ወርቅ ሁለት ዲፕሎማ በማግኘት ከዓለም 59ኛ ከአፍሪካ 6ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቋን ከስፖርት ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.