Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የ11ኛ ዙር ሻለቃ ከደር ማሰልጠኛ ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የ11ኛ ዙር ሻለቃ ከደር ማሰልጠኛ ማዕከልን ጎበኙ።
በጉብኝቱ አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሁሴን ሀሺ፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዣዥ ረዳት ኮምሽነር መሀመድ አህመድ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ረዳት ኮምሽነር መሀመድ አህመድ እንደገለፁት የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በአዕምሮና በአካል የዳበረ ስነምግባር ያለው ልዩ ሀይል እንዲሆን በስልጠናው ላይ በሰፊው ትምህርት ለሰልጣኞቹ ተሰጥቷል ብለዋል።
ሰልጣኞቹ ስልጠናውን ከጨረሱ በኋላም የክልሉን እና የሀገራቸውን ዳር ድንበር በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በስልጠና ላይ የሚገኙ ወጣቶች ስልጠናቸውን ሲጨርሱ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ነፃ እንዲሆኑና ህዝባቸውን በትጋት በማገልገል ለክልሉ እንዲሁም ለሀገሪቱ ሰላም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
እንዲሁም የክልሉን ልዩ ሀይል ለማዘመንና የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ እንደሆነ መግለፃቸውን የሶማሌ ክልል ቴሊቪዥን ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.