Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ከአለም ምግብ ፕሮግራም የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከአለም ምግብ ፕሮግራም የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚካኤል ደንፎርድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ሁኔታ ዙሪያ መምከራቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
አቶ ሙስጠፌ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለችግር የተዳረጉ ዜጎችን ለመታደግ አስፈላጊውን የምግብ እርዳታ በተገቢው ፍጥነት ማዳረስ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.