Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ።

የኮሚሽኑ አባላት ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር ባደረጉት ውይይት ከላይ እስከ ታች ያለው የመንግስት መዋቅር የኮሚሽኑን ስራ ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው፥ የኮሚሽኑን ስራ ለማገዝ መንግስት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ኦሮሚያ ከትግራይ ክልል በስተቀር ሁሉንም ክልሎች የምታዋስን በመሆኑ መልካም ጉርብትናን ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመጥቀስም ኮሚሽኑ የቀሩ ቀዳዳዎችን ለመሙላት ጠንክሮ እንደሚሰራ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ከድንበር እና ማንነት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ሳይንሳዊ፣ ግልፅ፣ አሳታፊ እና አቃፊ የሆነ ጥናት በማካሄድ የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ለኮሚሽኑ ከተሰጡ ስልጣኖች ውስጥ አንዱ እንደሆነ በውይይቱ መነሳቱን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.