Fana: At a Speed of Life!

አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ቡድን ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን በአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ቤት ደንፎርድ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ አቶ ንጉሱን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ተሳትፈዋል፡፡
አቶ ንጉሱ የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ እያደረገ ላለው ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማስፋት ኮሚሽኑ ለሚሰራቸው ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በዲጂታል ኢኖቬሽን ማልማት ፣ ወጣት መር ስራዎችን ለማጠናከር ፣ለሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ግንባታ እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር ባንኩ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንት ቤት ደንፎርድ በበኩላቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቹ የሥራ ዕድሎችን ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች ለማመቻቸት በቅንጅት መሥራታቸውን አድንቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የሥራ ዕድል ፈጠራን በተጠናቀረ መልኩ ለመምራት ኮሚሽኑን ማቋቋሙ መልካም ተሞክሮ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚመራው የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንቨስትመንት መሪ ኮሚቴ እስከ የፌዴራልና የክልሎች የሥራ ዕድል ፈጠራ አካላት የጋራ መድረክ ያሉት የቅንጅት መድረኮች ባንኩ ወጣቶችን በሁሉም ሴክተር ባሉ የሥራ ዕድሎች ለማካተት ከሚከተለው “የሥራ ለወጣቶች ስትራቴጂ” ጋር የሚጣጣም መሆኑን አስረድተዋል።
ውይይቱ አጋርነቱን በፍጥነት ወደ ትግበራ ደረጃ እንዲሸጋገር በመስማማት መጠናቀቁን ከ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.