Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ተገለፀ።

አቶ አሸብር በቀድሞ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በሜካኒካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የተቀበሉ ሲሆን፥ ከብሪታንያ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ቢዝነስ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

በምህንድስና ከተመረቁ በኋላም በበደሌ ቢራ ፋብሪካ ጀማሪ ሜካኒካል ኢንጂነር የስራ መደብ ላይ አገልግለዋል።

በ1996 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቀጥረው በጊምቢ -መንዲ – አሶሳ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ሰርተዋል።

እንዲሁም በተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከጥር 1997 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ዓመት መሪ መካኒካል ኢንጂነር ሆነው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችን በመቆጣጠር ተቋሙን አገልግለዋል።

ከግንቦት 2003 ዓ.ም ጀምሮም የገባ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ይህን ኃላፊነት እስከተቀበሉበት ቀን ድረስ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ስራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አቶ አሸብር ባልቻ ከየካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮም ተቋሙን በዋና ስራ አስፈፃሚነት እንዲመሩ በተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ መሾማቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.