Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻድሊ ሃሰን በአሶሳ ከተማ ከሚገኙ የጉሙዝ ብሔረሰብ ተወላጆች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ ፣መስከረም 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰንና ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ አቶ ጌታሁን አብዲሳ በአሶሳ ከተማ ከሚገኙ የጉሙዝ ብሔረሰብ ተወላጆች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

ውይይቱ “የጸረ-ሠላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ በተጠናከረ አብሮነት በመግታት ሠላምና ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ-ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

መድረኩ በተለይም በመተከልና ካማሺ ዞኖች እየተፈጠሩ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በጋራ በመሆን በዘላቂነት ከመፍታት ባለፈ፣ በክልሉ የቆየውን አብሮነትና ወንድማማችነት በማጠናከር ሠላምና ልማትን ለማስቀጠል ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በመድረኩ የብሔረሰቡ ተወላጅ የሃገር ሽማግሌዎች በማወቅም ሆነ በማለማወቅ የጸረ-ሠላም ኃይሎችን ተልዕኮ የሚያስፈጽሙ ወጣቶች ይህንን እኩይ ተግባር በመተው ወደ ሠላማዊ ቤተሰቦቻቸውና ወደልማት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ጠቁመው ከብሔረሰቡ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተካሄዱ ያሉ የውይይት መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለፃቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

በሁለቱ ዞኖች የሚስተዋሉ የጸረ-ሠላም ኃይሎች እንቅስቃሴ እና እየፈጸሙት ያለው እኩይ ተግባር የጉሙዝ ሕዝብን እንደማይወክልም በመድረኩ ተጠቀሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.