Fana: At a Speed of Life!

አቶ አዲሱ አረጋና የስፖርት ቤተሰቦች ሱሉልታ የሚገኘውን የኦሮሚያ ስፖርት አካዳሚ ግንባታ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋና የስፖርት ቤተሰቦች ሱሉልታ የሚገኘውን የኦሮሚያ ስፖርት አካዳሚ ግንባታ ጎበኙ።

የስፖርት አካዳሚዊ ግንባታ 90 በመቶ ደርሷል።

ግንባታው ከተጀመረ አምስት ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን ስራው 90 በመቶ መገባደዱን በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል።

አካዳሚው የተማሪዎችና መምህራን መኖሪያና መማሪያ ክፍሎች እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን አካቷል።

አካዳሚው 13 የስፖርት አይነቶችን ማሰልጠን የሚያስችልና 800 ሚሊዮን ብር የተበጀተለት ሲሆን በ20 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው።

በጉብኝቱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉና የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለን ጨምሮ የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል፤ በአካዳሚው የአካል ብቃት እንቅስቃሴም አድርገዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.