Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኢሳያስ ጅራ የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ሆነው መመረጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

የመካከለኛውና ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ማህበር/ሴካፋ/ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የአባል ሀገራቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቶች በተገኙበት በኡጋንዳ ካምፓላ በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይም ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት ሴካፋን የሚመሩ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት መርጧል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ሆነው የተመረጡ ሲሆን የታንዛኒያው ዋለስ ካሪያ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.