Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ዋና አስተባባሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ዋና አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ ጋር ተወያዩ።

ሃላፊዎቹ በሰብዓዊ ድጋፍ ዙሪያ በኒውዮርክ ተገኝተው መክረዋል።

በምክክሩም በሁሉም አካባቢዎች የሰብዓዊ አገልግሎት ለሚሹ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ በእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በፍጥነት መፍታት እንደሚገባ አቶ ደመቀ መኮንን አመልክተዋል።

በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ተከትሎ በአጎራባች አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች ለችግር ተጋላጭነታቸው እየጨመረ በመምጣቱ ሁሉዓቀፍ የሰብዓዊ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እንደሚጠይቅም ጠቁመዋል።

በሁሉም አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖችን በተሟላ አግባብ ተደራሽ ለማድረግ በእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በፍጥነት መፍታት እንደሚገባም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት እና አቅርቦት ባለው መስተጋብር የሚገጥሙ ክፍተቶችን ለመድፈን ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠይቅ አስምረውበታል።

ሁሉዓቀፍ የሰብዓዊ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የሚያደርገውን ርብርብ የዓለምአቀፉን ማህበረሰብ ሚዛናዊ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

ጽህፈት ቤቱም በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ከመንግስት ጎን በመቆም ለሚያደርገው ድጋፍም አቶ ደመቀ አመስግነዋል።

በውይይቱ መንግስት ለሰብዓዊ አገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ ባደረገው ርብርብ ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ጉዳዮች እንደተሻሻሉ የጋራ ግንዛቤ መያዙን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.