Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ፣ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ፣ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዮዬ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን÷ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት ያለውን አቋም በተመለከተ ለኮሚሽነሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ፣ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ችግር በውይይት ለመፍታት  የጀመራቸውን ጥረቶች እና ሀገር አቀፍ የምክክር ኮሚሽን አቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አድንቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የተፈጠረው ውዝግብ የሚያሳስብ መሆኑን የገለፁት  አምባሳደር ባንኮሌ÷ ኢትዮጵያ ውጥረቱን ለማረጋጋት የወሰደችው አወንታዊ እርምጃ የሚደነቅ ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን÷ በሱዳን መንግስት የተፈጠረው ትንኮሳ የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኘነት የማይመጥን መሆኑንም አስረድተዋል።

በዚህ ግጭት ሱዳን  ጉዳዩን አህጉራዊውን ተቋም የአፍሪካ ኀብረት አልፋ  ወደ መንግስታቱ ድርጅት መውሰዷ  ግጭቱን ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ያላትን ፍላጎት ያሳያል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.