Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ከሆኑት ማውሪን አቼንጌ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው ሕገ-ወጥ ፍልሰትን ለመግታት ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለውን ርምጃ በተመለከተና ወደ አገራቸው የተመለሱ ዜጎችን ፍላጎት በመቅረፍ ረገድ መክረዋል፡፡
በሌላ በኩል አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ መንግስት ለስደት መንስኤ የሆኑትን ምክንያቶች በመቅረፍ ረገድ እየወሰዳቸው ያለውን ርምጃዎች ለተወካይዋ አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የፌደራል መንግስት ከክልሎች ጋር በህገ-ወጥ ስደት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
እንዲሁም እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ካሉ ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የስደተኞችን መብትና ፍላጎት ለማስጠበቅ የሚደረግ ትብብር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ተወካይዋ በበኩላቸው ተቋሙ የኢትዮጵያ ስደተኞችን ፍላጎቶች ለመፍታትና እንዲሁም ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.