Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ከተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው ድርጅቱ በፈረንጆቹ 1984 ጀምሮ በሀገራችን የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ እና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትና ምላሽ አቅም እንዲጎለብት ላደረገው ውጤታማ ሥራ አቶ ደመቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ይሁን አንጂ በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በዋና መስሪያ ቤቱ ደረጃም ሆነ በሀገሪ ውስጥ ወኪል ጽህፈት ቤት በኩል በሚፈለገው ደረጃ ድጋፍ አለማድረጉን ጠቁመዋል፡፡
በትግራይ ክልል ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ ታዓማኒነት የሌላቸውን መግለጫዎችንና ሪፖርትቶችን በማቅረብ ድርጅታቸው ለተጫወተው አሉታዊ ድርጊት የኢትዮጵያን መንግሰት ያሳዘነ መሆኑንም አስድተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.