Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባ አንድ ላይ እንዲገናኙ ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ አፈፃፀሙን ለመመልከት በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባ አንድ ላይ እንዲገናኙ ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ አፈፃፀሙን ለመመልከት በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተወካይም ቀርበው ትእዛዙ መፈፀሙን አብራርቷል።

እነ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባም ትእዛዙ መፈፀሙን ገልፀዋል።

የአቶ ሀምዛ አዳነ (ቦረና) እና የአቶ ሸምሰዲን ጠሃ ጠበቃ ለችሎቱ ደንበኞቹ 30 ደቂቃ ብቻ አየር እያገኙ መሆኑን በመግለፅ፤ ከ30 ደቂቃ በላይ የፀሃይ ብርሃን እና አየር እንዲያገኙ ትእዛዝ እንዲሰጥለት ጠይቋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም በቂ አየር እና የፀሃይ ብርሃን እንዲያገኙ ትእዛዝ ሰጥቷል።

 

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.