Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ ለደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር መንግስት በህወሃት ውስጥ ባለው ቡድን ላይ እየተወሰደ ከሚገኘው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ገዱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከን መልዕክትም ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር አቅርበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ በዚህ ወቅት እየተወሰደ የሚገኘው ህግን የማስከበር እርምጃ የሉዓላዊ መንግስት ሃላፊነት ነው ብለዋል።

የፌዴራል መንግስት እየወሰደ የሚገኘውን ዘመቻ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱንም አቶ ገዱ ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በበኩላቸው ደቡብ ሱዳን በሉዓላዊነቷ የቆመችው ኢትዮጵያ በሰራቸው ስራም ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም የደቡብ ሱዳን ህዝብ እና መንግስት ሁልጊዜም ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን ይቆማሉ ብለዋል።

በተመሳሳይ አቶ ገዱ ከደቡብ ሱዳን የድህነነት ተቋም ሀላፊ አኮል ኮር ጋር የተወያዩ ሲሆን ለሃላፊው ተመሳሳይ መልዕክት አድርሰዋል።

እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ከተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኮንማደሮች ጋርም ምክክር ማድረጋቸው ነው የተገለፀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.