Fana: At a Speed of Life!

አንደኛው ዙር ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና ሙግት መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንደኛው ዙር ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና ሙግት መድረክ በሶስት ክልሎች ተካሄዷል፡፡

ምክንያታዊና በእውቀት ላይ የተመሰረተ የወጣት ማህበረሰብ መገንባትን ዓላማው ያደረገና ምሁራን ወጣቶች የሚሳተፋበት ነጻ የውይይትና ሙግት መድረክ በኦሮሚያ፣ በሶማሌና በሲዳማ ክልሎች የተካሄደ ሲሆን በነገው እለትም በአማራ ክልል ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

መድረኩ በሁሉም ክልሎች የሀገረ መንግስት ግንባታ እና የወጣቱ ሚና በሚል ርዕስ መዘጋጀቱን ከብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ በምሁራን ጽሁፍ አቅራቢነት የትኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ ያላቸው ወጣቶች የሚሳተፉበትና ነጻ መድረክ ሲሆን፥ የሀገረ መንግስት ግንባታ ምንነት፣ የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ያለበት ደረጃ እና ትምህርት የሚቀሰምባቸው ጉዳዮች፣ የሌሎች ዓለማት ልምድ እና የተጠናከረ ሀገረ መንግስት ግንባታን ለማረጋገጥ ከወጣት ምሁራን የሚጠበቀው ሚና ላይ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በሲዳማ ክልል በተዘጋጀው የምክንያታዊ ወጣቶች የክርክርና ሙግት መድረክ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሐም ማርሻሎን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የከተማ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.