Fana: At a Speed of Life!

አንዲት እናት 3 ልጆችን በሠላም ተገላገለች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ ዶቃቂት ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ትዝታ ንጉሴ 2 ሴቶች እና 1 ወንድ ልጅ በሠላም ተገላግላለች፡፡

ወይዘሮ ትዝታ የሕክምና ክትትል ስታደርግ በቆየችበት ደብረ-ሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መውለዷም ነው የተገለጸው፡፡

ወይዘሮ ትዝታ ሦስት ልጆች በሠላም በመገላገሏ ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች፡፡

ከዚህ ቀደም መንታ ልጆች በሰላም መገላገሏንም ገልጻለች፡፡

ሦስት ልጆችን በአንድ ጊዜ የመውለድ አጋጣሚ ያልተለመደና በሆስፒታሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረ እንደሆነ አዋላጅ ነርስ ሐብታሙ ታዬ ጠቁመዋል፡፡

በአልትራሳውንድ ምርመራ ሦስት ልጆችን ማርገዟ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ የጤና ምርመራና ክትትል በመደረጉ ልጆቿን በሠላም መገላገሏን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

እናትና ሕጻናቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.