Fana: At a Speed of Life!

አንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ስለኢትዮጵያ የሚያወጡት ዘገባ ከጋዜጠኝነት መርህ ያፈነገጠ መሆኑን ምሁራን ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያን በሚመለከት የሚያሰራጩት ዘገባ ከጋዜጠኝነት መርህ ያፈነገጠ መሆኑን የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ምሁራን ገለጹ።
አፍሪካን የሚወክል ጠንካራ ሚዲያ ሊቋቋም እንደሚገባም ነው ምሁራኑ ያነሱት፡፡
ገለልተኝነትና ትክክለኝነት ከጋዜጠኝነት አንኳር መርሆች መካከል ዋነኞቹ ቢሆኑም÷ የተወሰኑ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ግን ከዚህ በተቃራኒው ሆን ብለው የተዛቡ መረጃዎችን እያሰራጩ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት መምህር ዶክተር ሙሉቀን አሰግደው እንዳሉት÷ አንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ለአሸባሪው ህወሓት የሚያደላ ዘገባ እየሰሩ ነው።
ይህም መሰረታዊ ጋዜጠኝነት መርህን የሚጥስ እንደሆነ የገለጹት ምሁሩ÷ በስራዎቻቸው አንዱን አካል ተጠቂ ሌላውን ደግሞ አጥቂ አድርገው መሬት ላይ ያለውን እውነታ በካደ መልኩ እየዘገቡ ነው ብለዋል፡፡
ቴሌግራፍ የተሰኘው የዜና አውታር በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአርሲ አካባቢ የስንዴ ምርት በጎበኙበት ወቅት ያደረጉትን ንግግር አዛብቶ ያቀረበበትን ሁነት ለአብነት አንስተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.