Fana: At a Speed of Life!

የሕንዱ የባቡር ኩባንያ ዝሆኖችን ለመታደግ የንብ ድምፅን እየተጠቀመ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕንዱ የባቡር ኩባንያ ዝሆኖችን ከአካባቢው ለማራቅ የመንጋ ንብ ድምፅን እንደ ማስፈራሪያ እየተጠቀመ ነው።

በሃገሪቱ ሰሜን ምስራቅ መንገድ የሚያቋርጡ ዝሆኖች በባቡር በሚደርስባቸው ግጭት ሳቢያ ለሞት እየተዳረጉ እንደሚገኙ ኩባንያው ገልጿል።

ይህን ለማስቀረት እና ዝሆኖቹን ለመታደግም የመንጋ ንብ ድምጽን በአምፕሊፋየር በመልቀቅ ዝሆኖቹን ከአካባቢው ለማራቅ እየተጠቀመበት መሆኑን ገልጿል።

ይህን የሚያደርገው ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች በስፍራው የዝሆን መንጋ ሲመለከቱ ለኩባንያው ሰራተኞቸ የሚሰጡትን መረጃ መነሻ በማድረግ መሆኑንም አስታውቋል።

በተፈጥሮ ዝሆኖች የንብ መንጋ እንደማይወዱ ይነገራል።

ኩባንያው ታዲያ አዲሱ አሰራር ዝሆኖችን ከሞት ለመታደግ አዋጭ መንገድ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

 

ምንጭ፦ ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.